አዋሽ ባንክ በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች 30 ሚሊዮን ብር ለገሰ

በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በተፈጥሯዊና ሰዉ ሰራሽ ችግሮች ሳቢያ ለተለያዩ ጉዳቶች ለሚጋለጡ ዜጎች ድጋፍ በማድረግ የሚታወቀዉ አዋሽ ባንክ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የሰላሳ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።
አዋሽ ባንክ ባለፈዉ ዓመትም በቦረና ጉጂ ዞኖች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖችና የብር 60 ሚሊዮን ብር ለግሷል።
በተመሳሳይ ሁኔታ በማህበራዊ ኃላፊነት መወጫ መርሐግብሩ በምዕራብ ኦሮሚያ ተከስቶ በነበረዉ የእርስ በርስ ግጭት ተፈናቅለዉ ለነበሩ ዜጎችና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ንፋስ ቀላቅሎ በጣለዉ ከባድ ዝናብ ቤት ለፈረሰባቸዉ አባወራዎችም የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

May 20, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
56.9985 58.1385
GBP
68.8367 70.2134
EUR
61.7864 63.0221
AED
14.0421 14.3229
SAR
13.7538 14.0289
CHF
59.8369 61.0336

Exchange Rate
Close