በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች የራሱን ህንፃ በመገንባት የሚታወቀው አዋሽ ባንክ በአምቦ ከተማ ከምድር በታች ቤዝመንት ያለው ባለ ሰባት ወለል (G+7) አዲስ ዘመናዊ ህንፃ ለመገንባት መሳይ ኦሊ ከተሰኘና በግንባታ ዘርፍ ከፍተኛ ልምድ ካለው የህንጻ ተቋራጭ ድርጅት ጋር የውል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
ለአምቦ ከተማ የመልካም ገፅታ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው የሚታመነው አዲሱ የአዋሽ ባንክ አምቦ ቅርንጫፍ ህንፃ ግንባታም በፍጥነት እንደሚጀመርና በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚውል የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው በፊርማ ሥነ ስነስርዓቱ ላይ ተናግረዋል፡፡