የQAXALEEWWAN (ቀጠሌዋን) የስራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊዎች ሽልማታቸውን ተረከቡ

ለተከታታይ ሳምንታት በOBN ቴሌቪዥን በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ሰፊ የስርጭት ሽፋን በነበረውና QAXALEEWWAN (ቀጠሌዋን) በተሰኘው የስራ ፈጠራ ውድድር ላይ በመሳተፍ አሸናፊ ለሆኑ ተወዳዳሪዎች በዳኞች ውሳኔ መሰረት ከ 1 – 6ኛ ደረጃዎች ውስጥ ለገቡ አሸናፊዎች ለእያንዳንዳቸው ማለትም ለ1ኛ ደረጃ አሸናፊ የብር 1 ሚሊዮን፣ 2ኛ ለወጣው አሸናፊ የብር 700 ሺህ፣ ለ3ኛ የብር 500 ሺህ፣ ለ4ኛ የብር 300 ሺህ ፣5ኛ ደረጃ ላይ ለሚገኘው ተወዳዳሪ የብር 200 ሺህ እንዲሁም 6ኛ ለወጣው ብር 100 ሺህ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል እንዲሁም ከዋስትና ነፃ እስከ ብር 5 ሚሊዮን ብድር እንደየ ፕሮጀክታቸው ሁኔታ ተመቻችቶላቸዋል ፡፡
ባንኩ በዛሬው እለት በስካይ ላይት ሆቴል ባካሄደው የመርሐ ግብሩ የማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው እንደገለፁት የኮርፖሬት ማህበራዊ ሃላፊነት አካል የሆነው ስራ ፈጣሪዎችን የሚያበረታታው ይህ ፕሮጀክት ለወደፊቱም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅሰዋል፡፡ በሥነ ሥርዓቱ ላይ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችን ጨምሮ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

May 07, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
56.9375 58.0763
GBP
68.3661 69.7334
EUR
61.3103 62.5365
AED
14.0267 14.3072
SAR
13.7380 14.0128
CHF
60.0302 61.2308

Exchange Rate
Close