አዋሽ ባንክ “በአዋሽ ይቆጥቡ ይቀበሉ ይሸለሙ” አሸናፊ ለሆኑ እድለኞች ያዘጋጀዉን ሽልማት አስረከበ

አዋሽ ባንክ በ10ኛው ዙር “በአዋሽ ይቆጥቡ ይቀበሉ ይሸለሙ” የሎተሪ መርሐ ግብር አሸናፊ ለሆኑ እድለኞች ያዘጋጀዉን ሽልማት አስረክቧል፡፡

ለአስረኛው ዙር መርሐ ግብር የተዘጋጁት የሽልማት ዓይነቶች በአራት ደረጃዎች የተከፋፈሉ ሲሆን ለአንደኛው ዕጣ የተዘጋጀው የሽልማት ዓይነት አንድ ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል ሱዙኪ ዲዛየር መኪና የሎተሪ ቁጥር 00021413447 የያዙት አቶ ታስልኦች ኳንግ ቤል በጋምቤላ ከተማ ጋምቤላ ኒው ላንድ ቅርንጫፍ የባንክ አገልግሎት ባገኙበት ወቅት በተሰጣቸው የሎተሪ ዕጣ ቁጥር አሸናፊ ሆነዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ለ2ኛ እጣ የተዘጋጁት (ሶስት ዕጣዎች) እያንዳንዳቸው ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ መኪኖች ፣ ጨምሮ በርካታ ባለ 43 ኢንች ኤልኢዲ ቴሌቪዥኖች እና የሞባይል ስልክ ቀፎዎችን ዕጣ ለወጣላቸው ዕድለኞች ተበርክቶላቸዋል፡፡

አዋሽ ባንክ ያዘጋጀው የሎተሪ መርሐ ግብር የማህበረሰቡን የቁጠባ ባህል በማሳደግ የተሻለ የኑሮ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ግንዛቤን ከመፍጠሩም ባሻገር ለአገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት አስፈላጊ እና ወሳኝ የሆነውን የውጭ ምንዛሪ ፍሰት በሕጋዊ መንገድ እንዲመጣ በማድረግ የሚገኘውም የውጭ ምንዛሪ ለአገራችን ልማትና ዕድገት እንዲውል ለማስቻል የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ረገድ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ተጠቁሟል፡፡

Sep 21, 2023 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
55.1948 56.2987
GBP
65.1720 66.4754
EUR
59.0308 60.2114
AED
13.5981 13.8701
SAR
13.3154 13.5817
CHF
58.7571 59.9322

Exchange Rate
Close