ኢጃራህ ደንበኛዉ መግዛት የሚፈልገዉን ንብረት ባንክ ገዝቶለት ለደንበኛዉ በማከራየት ደንበኛዉ በተራዘመ ጊዜ ለንብረቱ የኪራይ ክፍያ እየከፈለ በመጨረሻም የንብረቱን ዋጋ በኪራይ ክፍያ ሲጨርስ የራሱ የሚያደርግበት አካሄድ ነዉ፡፡ በዚሁ መሠረት ደንበኛዉና ባንኩ በሚኖራቸዉ ዉል መሠረት ደንበኛዉ ንብረቱን በስተመጨረሻ የራሱ ያደርጋል፡፡
የኢጃራህ መሠረታዊ ህጎች፡-
Ø ንብረቱ የኪራዩ ጊዜ እስኪያበቃ ንብረትነቱ የባንኩ ይሆናል፤
Ø የኪራዩ ጊዜ ገደብ በግልጽ ይቀመጣል፤
Ø የኪራዩ ጊዜ የሚጀምረዉ ንብረቱ መከራየት ከጀመረበት ዕለት አንስቶ ይሆናል፡፡