በባንኩና በደንበኛዉ መካከል በሚኖር የደንበኝነት ግንኙነት ነዉ፡፡ ደንበኛዉ ገንዘቡን ሲያስቀምጥ ባንኩ የሸሪኣ ህግን ተከትሎ ቢዝነስ ይሰራበታል፡፡ የሚገኘዉ ትርፍም ሆነ ኪሣራ የሚኖር ከሆነ ባንኩና ደንበኛዉ በሚያደርጉት ስምምነት መሠረት የሚከፋፈሉት ይሆናል፡፡
ጠቀሜታ፡-
- የገቢ ክፍፍል፤
- ከፍተኛ መጠን ያለዉ ኢንቨስትመንት ለማካሄድ፤
- የገንዘብ ፍሰት ሁኔታ መረጋጋት፡፡
ገጽታ፡-
- ግለሰቦች ይህንን ሂሳብ ይመርጡታል፤
- ለካፒታል አስተዳዳር ያመቻል፤
- የትርፍ ክፍፍል መብት ያስገኛል፤
- ኪሳራ ሲያጋጥም በመካፈል ለማቅለል ይረዳል፡፡
ሂሳቡን ለመክፈት አስፈላጊ ዶክመንቶች፡-
- የተሟላ የሂሳብ መክፈቻ ፎርም መሙላት፤
- የሂሳቡ ባለቤት ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸዉ ጉርድ ፎቶግራፎች፤
- አንድ ጉርድ ፎቶግራፍ፤
- የታክስ ከፋይነት መለያ ቁጥር ፤መታወቂያ፤ፓስፖርት፤የሊቀመንበር የማስረጃ ወረቀት፡፡