አዋሽ ባንክ ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ የብር 70 ሚሊዮን አክሲዮን መግዛቱን አስታወቀ፡፡

አዋሽ ባንክ የኢትዮጰያ መንግስት ለፋይናንስ ተቋማት ባመቻቸው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ የአክሲዎኖች ግዥ ዕድል መሰረት የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በተደረገ ጋዜጣዊ መግለጫ የብር 70 ሚሊዮን አክሲዮን መግዛቱን አስታውቋል፡፡
የባንካችን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደተናገሩት በገበያ መር የኢኮኖሚ ሥርዓት ውስጥ የካፒታል ገበያ መመሥረትና ማደግ ለኢንቨትመንት የሚሆን መዋዕለ ነዋይን በማሰባሰብ ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ ድረሻ እንደሚኖረው በመግለጽ ኢትዮጵያ ለኢንቨስተመንት ምቹ የሆነ የፖሊሲ ማዕቀፍ፣ የተፈጥሮ ሃብትና ወጣት የሰው ኃይል ቢኖራትም የካፒታል ውስንነት በመኖሩ ምክንያት የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ የራሱን አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳረፉን ገልጸዋል፡፡
በካፒታል ገበያው ማቋቋሚያ አዋጅ መሠረት የኢትዮጵያ ሰክዩሪቱ ኤክስቼንጅ በሼር ካምፓኒ ደረጃ ተቋቁሞ በሀገራችን ካሉት ተቋማት የአክሲዮኑ አባል እንዲሆኑ ቅድሚያ ከተሰጣቸው ዘርፎች መካከል የፋይናንስ ተቋማት የመጀመርያ ረድፍ መያዙን የኢትዮጵያ ሰክዩሪቱ ኤክስቼንጅ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ጥላሁን እስማኤል በመግለጫው ላይ ገልጸዋል።
እንደሚታወቀው አዋሽ ባንክ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ፣ ላለፉት 29 ዓመታት ዘመናዊና አስተማማኝ የባንክ አግልግሎቶችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ለአገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት እና ለሕብረተሰባችን የኑሮ መሻሻል የበኩሉን አስተዋጽኦ በማበርከት እስካሁን የዘለቀ ሲሆን አሁንም በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡

Apr 30, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
56.9193 58.0577
GBP
68.1105 69.4727
EUR
61.0061 62.2262
AED
14.0233 14.3038
SAR
13.7339 14.0086
CHF
59.6356 60.8283

Exchange Rate
Close