አዋሽ ባንክ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

በስምምነቱ መሠረት የኤልክትሪክ ፍጆታ ክፍያ በአዋሽ ባንክ የክፍያ አማራጮች እንዲሳለጥ እና ሌሎችም የፋይናንስ ተቋማት ደንበኞች ያለ ምንም ውጣ ውረድ ክፍያቸውን ከሚፈልጉት የፋይናንስ ተቋም መክፈል እንዲችሉ የሚያደርግ መሆኑን ተጠቁሟል።
አዋሽ ባንክ አገልግሎቱን ይበልጥ ምቹና ቀልጣፋ ለማድረግ ዘመኑን የዋጁ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ግዥ በመፈፀም አዲስ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶችን በማስፋፋት ላይ ሲሆን የደንበኞቹን አስተያየት፣ ጥያቄ እና ቅሬታ ከግምት ውስጥ በማስገባት በየጊዜው የአሰራር ሂደቶቹን እያሻሻለ የደንበኞቹን ፍላጐት በማርካት ታላቅ አመኔታን እያተረፈ መሆኑን የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው በፊርማው ሥነ ሥርዓት ላይ ገልጸዋል፡፡

Apr 30, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
56.9193 58.0577
GBP
68.1105 69.4727
EUR
61.0061 62.2262
AED
14.0233 14.3038
SAR
13.7339 14.0086
CHF
59.6356 60.8283

Exchange Rate
Close