አዋሽ ባንክ “አዋሽ ለሁሉም” የተሰኘ ዲጂታል አነስተኛ የብድር አገልግሎት ይፋ አደረገ

ህዳር 24 ፣ 2016 ዓ.ም (አዲስ አበባ)፣ አዋሽ ባንክ “አዋሽ ለሁሉም” የተሰኘ አነስተኛ የብድር አገልግሎት የሚያገኙበት ዲጂታል የብድር አገልግሎት በዛሬው እለት የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት አካላት እና እንግዶች በተገኙበት በኢሊሊ ሆቴል ይፋ አድርጓል።

በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፉና ዘመኑን የዋጁ የባንክ አገልግሎቶችን በመስጠት ተደራሽነቱን በማስፋት ላይ የሚገኘው አዋሽ ባንክ የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት ደንበኞች ባሉበት ሆነው አነስተኛ የብድር አገልግሎት የሚያገኙበት “አዋሽ ለሁሉም” የተሰኘውን አገልግሎት እንዲሁም የሳኮስ አይቲ ሶሉዩሽን (SACCOs IT Solution) ቴክኖሎጂ ዛሬ ይፋ ሆኗል።

በሥነ-ስርዓቱ ላይ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው እንደገለፀት አዋሽ ባንክ በኢንዱስትሪው ውስጥ ያለውን የመሪነት ስፍራውን ይዞ እንዲቀጥልና የደንበኞቹን ፍላጎት ለማሟላት በየጊዜው አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ እንደሚያደርግ አመላክተዋል፡፡

Apr 30, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
56.9193 58.0577
GBP
68.1105 69.4727
EUR
61.0061 62.2262
AED
14.0233 14.3038
SAR
13.7339 14.0086
CHF
59.6356 60.8283

Exchange Rate
Close