የድርጅቱ ፕሮፋይል

ስለ አዋሽ ባንክ

በኢትዮጵያ ፈር ቀዳጅ የግል ባንክ  የሆነው አዋሽ ባንክ የተመሰረተው የሶሻሊስት ስርዓተ መንግስት ውድቀትን ተከትሎ በአገራችን ለመጀመርያ ጊዜ ተግባራዊ በተደረገው የነፃ ገበያ መር የኢኮኖሚ ፖሊሲ መሰረት እ.ኤ.አ ህዳር 10 ቀን 1994 በ486 ባለራዕይ መስራች ባለአክሲዮኖች በብር 24.2 ሚሊዮን የተከፈለ ካፒታል ሲሆን የባንክ ሥራ የጀመረው እ.ኤ.አ.የካቲት 13 ቀን 1995  ነዉ።

ባንኩ ሥራ ከጀመረ ወዲህ አመርቂ ዕድገት አስመዝግቧል እያሰመዘገበም ነዉ። ዓለም አቀፋዊና የአገር ውስጥ ተግዳሮቶች እንዳሉ ሆነው፣ አዋሽ ባንክ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ የግል ባንኮች የላቀ የአሠራርና የፋይናንስ አፈጻጸም አሳይቷል። አዋሽ ባንክ የካፒታል መሰረቱን፣ የቴክኖሎጂ አቅሙን፣ የሰው ሃይሉን እና የደንበኞችን መሰረት በማጠናከር የላቀ ውጤት ለማስመዝገብም እየሰራ ነው።

የባንካችን ስያሜ ኢትዮጵያ ውስጥ ከትናንሽ እስከ ትልቅ የመስኖ ልማት፣ የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ እና ለኢንዱስትሪ ስራዎች በስፋት አገልግሎት ላይ የሚውለው  የአዋሽ ወንዝ  ነው። በመሆኑም ልክ  አዋሽ ወንዛችን በአገር ልማት በግንባር ቀደምትነት እንደሚጠቀሰው ባንካችንም  የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የተሟላ የባንክ አገልግሎት በመስጠት  ለአገሪቱ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማበርከት በዘርፉ በግንባር ቀደምትነት ይተቀሳል፡፡ ስለሆነም የቁጠባ ባህልን በማበረታታት፣ የብድር አገልግሎት አቅርቦትን እና ቀልጣፋ እና ፈጣን የክፍያ ሥርዓቶችን በማመቻቸት ህዝቡን ማገልገል መርሃችን ነው።

የባንካችን ዋና እሴት አንዱ ተደራሽነት ነው። ሁልጊዜ በተለያዩ የአገልግሎት መስጫ ቻናሎች ተደራሽነታችንን ለማሻሻል እንጥራለን። በአሁኑ ጊዜ እኛ በሀገሪቱ ውስጥ ሰፊ የቅርንጫፍ አውታሮችን በመያዝ ትልቅ አሻራ ያለው እና ተደራሽ የግል ባንክ ነን። ከቅርንጫፍ ኔትወርኮች በተጨማሪ ለደንበኞቻችን የ24/7 አገልግሎትን በኤቲኤም፣ በፖስ ማሽኖች፣ በኢንተርኔት፣ በሞባይል እና በኤጀንሲ ባንኪንግ የተሟላ የባንክ አገልግሎት እንሰጣለን።

አዋሽ ባንክ ምንም እንኳን ለትርፍ የተቋቋመ የፋይናንስ ተቋም ቢሆንም ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት የሚታወቅ ነው።. በዚህም በኮርፖሬት የማህበራዊ ኃላፊነት መወጫ ፖሊሲው መሰረት  በትምህርት፣ በጤና፣ በሴቶችና ህፃናት፣ በወጣቶች እንዲሁም በተፈጥረአዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች  የተጎዱ አካባቢዎችን በመደገፍ፣ የአካባቢ እና ማህበራዊ ደህንነትን ለማሻሻል የገንዘብ ልገሳ እያደረገ ይገኛል። በዚህም በእሰካሁን የተደረጉ የፋይናንስ ድጋፎች  በማህበረሰቡ ላይ አወንታዊ ተፅእኖ ማምጣት ተችሏል፡፡

ስኬታችን የሚለካው በስትራቴጂያችን ውስጥ የተገለጹትን ድርጅታዊ ግቦቻችንን እና አላማዎች በማሳካት ነው። በዚህ ረገድ የ10-አመት ስትራቴጂካዊ ፍኖተ ካርታ ቀርፀን እ.ኤ.አ 2025 አዋሽ ባንክን ከምስራቅ አፍሪካ ምርጥ አስር ባንኮች አንዱ ማድረግ  በሚል መሪ ቃል ስራችንን ስንሰራ ቆይተናል። እስካሁን ያለን አፈጻጸም የሚያመለክተው ባንኩ ከ2025 በፊት እነዚያን ግቦች ማሳካት እንደሚችል ነው። አዋሽ ባንክ ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ በአብዛኛዎቹ ቁልፍ የፋይናንስ አፈጻጸም አመልካቾች ከአማካይ በላይ ዕድገት አስመዝግቧል፡፡ይህ ደግሞ  በእርግጥም አዋሽ ባንክ በአገሪቱ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የግል ባንኮች ብቸኛ ፈጣን ዕድገት አስመዝጋቢ መሆኑን የመያረጋግጥ ነዉ። ለዚህ አስደናቂ ስኬት ባለ ቤትም የዳይሬክተሮች ቦርድ ባለራዕይ አመራር፣ ቁርጠኛ የአስተዳደር ቡድን፣ ቁርጠኛ ሰራተኞች እና ታማኝ ደንበኞቻችን ናቸዉ።

ዋና ዋና ሴቶች

ተደራሽነት

ጥበብ

ተጠያቂነት

ማህበራዊ ኃላፊነት

 ታማኝነት

ስልታዊ ግቦቻችን እና ግቦቻችን በምኞት ላይ የተመሰረቱ ናቸው።

ራዕይ፡-

"ደንበኞች ዋጋ እንዳላቸው የሚሰማው ምርጥ እና ተመራጭ የፋይናንስ አገልግሎት አቅራቢ ባንክ መሆን"

ተልዕኮ፡

"እጅግ በጣም ተመጣጣኝ በሆነ ቴክኖሎጂ፣ ከፍተኛ ብቃት እና ተነሳሽነት ያላቸው ሠራተኞችን በመጠቀም ፈጠራ የታከለበት እና ተደራሽ የሆነ የባንክ አገልግሎት ለደንበኞች በመስጠት የባለ አክሲዮኖችን ዋጋ ማሳደግ እና በህብረተሰቡ ኑሮ ላይ በጎ ተፅዕኖ መፍጠር"

May 31, 2023 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
54.3041 55.3902
GBP
64.4469 65.7358
EUR
58.2683 59.4337
AED
13.3787 13.6463
SAR
13.1039 13.3660
CHF
57.4567 58.6058

Exchange Rate
Close