የዲያስፖራ የባንክ አገልግሎት 

  • ይህ አገልግሎት በዉጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና የዉጭ ሀገር ዜግነት ላላቸዉ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በዉጭ ገንዘብ ምንዛሪ ሀገራቸዉ ላይ የባንክ ሂሳብ ከፍተዉ እንዲያስቀምጡ የተመቻቸ አገለግሎት ነዉ፤
  • ግለሰቦችና በዉጭ ሀገር ዋና መሥሪያ ቤት ያላቸዉ ድርጅቶች ሂሳቡን ከፍተዉ ሊጠቀሙበት ይችላሉ፤
  • ሂሳቡ ከሚከተሉት የገንዘብ ዓይነቶች ብቻ በአንዱ ሊከፈት ይችላል፡-
  • የአሜሪካ ዶላር፤
  • ፓዉንድ ስተርሊንግ፤
  • ዩሮ፤
  • በሌሎች ሀገር ምንዛሪ ተቀማጭ የሚደረጉ ገንዘቦች ማለትም በካናዳ ዶላር፣ ሳኡዲ ሪያል፣ የጀፓን የን፣ የአዉስትራሊያ ዶላር፣ እና ዩናትድ አረብ ኢምሬትስ ድርሃም የሚቀመጡ ገንዘቦች ከላይ ከተጠቀሱት ወደ አንዱ ገንዘብ ብቻ በሂሳቡ ባለቤት ምርጫ ተቀይረዉ ተቀማጭ ይደረጋሉ፡፡

.የመደበኛ ተቀማጭ ሂሳብ

  • ይህ ሂሳብ ወለድ ያለዉ ሂሳብ ሲሆን በማብቂያ ጊዜ ገደብ ስምምነት የሚከፈት ነዉ፤
  • ዝቅተኛዉ የማብቂያ ጊዜዉ ሶስት ወር ነዉ፤
  • ቀደም ሲል ከተገለጹት የገንዘብ አማራጮች በአማሪካ ዶላር መጠን 5 ዶላር እኩል በሚሆን መነሻ ገንዘብ ሂሳብ ይከፈታል፤
  • ለነዚህ ሂሳቦች ወለድ የሚከፈለዉ ገንዘቡ ቢያንስ ለሶስት ወራት በባንኩ ከቆየ ብቻ ነዉ፤
  • ለነዚህ ሂሳቦች የሚከፈል ወለድ ከታክስ ክፍያ ነጻ ነዉ፤
  • ባንኩ ሂሳቡ ሲከፈት ለከፈቱት ደንበኞች ሂሳቡን ከፍተዉ ገንዘብ ገቢ እንዳደረጉ የምሥክር ወረቀት ይሰጣቸዋል፤
  • ባንኮች በዉጭ ሀገር ገንዘብ በሚከፈቱ መደበኛ ሂሳቦች ላይ የራሳቸዉን የወለድ ምጣኔ በስምምነት እንዲያዘጋጁ ይፈቀድላቸዋል፡፡

አስፈላጊ ዶክመንቶች፡-

  • የማመልከቻ ቅጾች በአመልካቹ ተሞልተዉ መፈረም አለባቸዉ፤
  • ለኢትዮጵያዊያንና የዉጭ ሀገር ዜግነት ላላቸዉ ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን የታደሰ ፓስፖርት/መታወቂያ ካርድ፤
  • በጎረቤት ሀገራት ወይም በመካከለኛዉ ምሥራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና የዉጭ ሀገር ዜግነት ያላቸዉ ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያ ኤንባሲዎች የተረጋገጠ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ እነዚህ አስፈላጊ ዶክመንቶች ሁሉ በየዓመቱ በመታደስ ለባንኩ መቅረብ አለባቸዉ፡፡

.ሂሳቡን ስለመዝጋት

የሚከተሉት ሁኔታዎች የዲያስፖራ ሂሳብን ሊያዘጉ ይችላሉ፡-

  • በሂሳቡ ባለቤት ጥያቄ፤
  • የሂሳቡ ባለቤት የዉጭ ሀገር ሥራዉን አጠናቆ ኢትዮጵያ ዉስጥ መኖር ሲጀምር፤
  • ወደ ሂሳቡ የተላለፈ ገንዘብ በጥቁር ገበያ/ማጭበርበር/ ወይም የሽብር ተግባርን የሚደግፍ ሆኖ ሲገኝ፡፡

.ገንዘብ ወደ ሂሳቡ ገቢ የሚደረግባቸዉ መንገዶች

  • ከሚኖሩበት ቦታ በቀጥታ ወደ ሂሳቡ በባንኩ ስዊፍት አድራሻ፡-
  • በሂሳቡ ባለቤት፤
  • የሂሳቡ ባለቤት ሚስት የጋብቻ የምሥክር ወረቀት በማቅረብ፤
  • የሂሳቡ ባለቤት ሠራተኛ የሥራ ቅጥር ዉል በማሳየት፤
  • በሂሳቡ ባለቤት የተያዘ የቢዝነስ ሥራዉ አካል ወይም የአክሲዮን ማህበሩ አባል የአክሲዮን ስምምነት ዶክመንቱን በማሳየት፤
  • ሌሎች የሥራ ዉል ስምምነት የሚያቀርቡ ተቋማት ካሉ፤
  • የሂሳቡ ባለቤት ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የተፈረመና የታሸገ የዉጭ ሀገር ገንዘብ መግለጫ ደብዳቤ ካቀረበ ከ3,000 የአሜሪካ ዶላር እና ከዚያ የበለጠ መጠን ያለዉ የሌላ ሀገር ገንዘብ፤
  • በጎረቤት ሀገራት ወይም መካከለኛዉ መሥራቅ የሚኖሩ ባለ ሂሳቦች ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የተፈረመና የታሸገ የዉጭ ሀገር ገንዘብ መግለጫ ደብዳቤ ካቀረቡ 3,000 የአሜሪካ ዶላር እና የበለጠ መጠን ያለዉ የሌላ ሀገር ገንዘብ ወደ ሂሳባቸው ገቢ ማድረግ ይችላሉ፤
  • ከዉጭ ሀገር የመነጨ የቼክ ገንዘብ ገቢ፤
  • በግለሰቦችና ኢንተርፕራይዞች የተያዙ ከሀገር ዉጭ ባለዉ የዉጭ ሀገር ገንዘብ ሂሳብ ወደ ሂሳቡ ገቢ ማድረግ፤
  • በክፍያ ካርዶች/በገቢ ማድረጊያ ካርዶች /በወጪ ማድረጊያ ከርዶች/ ደረሰኝ፡፡
  • .የዉጭ ሀገር ገንዘብ ሂሳቦች ለሚከተሉት አገልግሎቶች ሊዉሉ ይችላሉ፡-

    • የሀገር ዉስጥ ክፍያ በብር ለመፈጸም፤
    • ኢትዮጵያ ዉስጥ በሚገኙ ባንኮች ወደሚገኙ የሌሎች ሀገሮች ገንዘብ ሂሳቦች በዉጭ ሀገር ገንዘብ ማስተላለፍን ይጨምራል፤
    • የሂሳቡ ባለቤት ያለዉ የንግድ ሥራ ፈቃድ ለዚህ ብቁ ከሆነ የላኪና አስመጪ የአገልግሎት ክፍያ የመሳሰሉ የዉጭ ሀገር ክፍያዎችን ለመፈጸም፤
    • የዉጪ ሀገር ገንዘብ ማስተላለፍ፤
    • የተሟላ አገልግሎት ያለዉ የጉዞ ፈቃድ ዶክመንት ኖሮት ለጉዞ መፈጸሚያ የሚዉል ገንዘብ ወጪ ለማድረግ፤
    • ባለዉ የምንዛሪ መጠን የዉጭ ሀገር ገንዘብን ወደ ብር ሂሳብ ለመቀየር፤
    • ሂሳቡ በሚከፈትበት ባንክ የሚከፈል ከሆነ ለባንኩ የአገልግሎት ክፍያ ለመፈጸም፤
    • ለብድር ወይም ለጨረታ ማስያዣ ለማቅረብ፡፡

    .ወደ ሂሳቡ በስዊፍት አድራሻ ገቢ ማድረግ ከተፈለገ ለላኪዉ ባንክ የሚከተሉትን ዝርዝር መረጃ ይስጡ፡-

    • የሂሳቡን ባለቤት ሙሉ ስም ከአዋሽ ባንክ ስም ጋር፤
    • የሂሳብ ቁጥር፤
    • ሂሳቡ የሚገኝበት የባንኩ ቅርንጫፍ ስም፤
    • የስዊፍት አድራሻ፡-AWINETAA

ከ forex ቢሮዎች ወይም ከማንኛውም የሀገር ውስጥ ምንጭ ወይም በአገር ውስጥ የሚገኝ የውጭ ምንዛሪ ለብድር እና/ወይም የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ ለመክፈት መዋል የለበትም።

  • ሂሳብ መክፈቻ ቅጹን ለመሙላት የሚያገለግለዉን መተግበሪያ ከበይነ መረብ ማዉረድ፡፡
  • ቅጹን በህትመት ያዉጡት፡፡ ተንቀሳቀሽ ሂሳብ ለመክፈት የሚያገለግለዉንም ቅጽ እዚሁ ላይ ያገኙታል፤
  • ቅጹን በጥንቃቄ በመሙላት ለቅርንጫፍ ባንኩ ያቅርቡ፡፡ወይም፡-
  • ከኢትዮጵያ ዉጭ በሚኖሩበት ቦታ ሂሳቡን ለመክፈት ከፈለጉ በአቅራቢያዎ ባሉ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዴስኮች በመገኘት ቅጹን ፤
  • ቅጹን ከሞሉ በኋላ በኢትዮጵያ ወይም በኤንባሲዎች የሚከፍቱት ሂሳብ የቁጠባ ሂሳብ ከሆነ ከአስፈላጊ ዶክመንቶች ጋር ማለትም የታደሰ ፓስፖርት፣ መታወቂያና ፎቶግራፎች ጋር ያቅርቡ፡፡
  •  
አስፈላጊ ዶክመንቶች፡-

  • የማመልከቻ ቅጾች በአመልካቹ ተሞልተዉ መፈረም አለባቸዉ፤
  • ለኢትዮጵያዊያንና የዉጭ ሀገር ዜግነት ላላቸዉ ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን የታደሰ ፓስፖርት/መታወቂያ ካርድ፤
  • በጎረቤት ሀገራት ወይም በመካከለኛዉ ምሥራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና የዉጭ ሀገር ዜግነት ያላቸዉ ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያ ኤንባሲዎች የተረጋገጠ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ እነዚህ አስፈላጊ ዶክመንቶች ሁሉ በየዓመቱ በመታደስ ለባንኩ መቅረብ አለባቸዉ፡፡

ዛሬውኑ ባሉበት ሆነው አካውንት ይክፈቱ

ተጨማሪ መረጃ?

8980
251 115-57-12-54
251 115-57-13-24
ይደውሉልን ከ ጠዋት 3- ማታ 11ሰአት ያገኙናል፡፡

ደንበኛ ኖት?

በአቅራቢያዎ የሚገኙ ቅርንጫፎችን ያግኙ ወይም ለበለጠ መረጃ ያኙን

መተግበሪያችን

የተማላ የሞባይል ባንኪንግ ለግል እና ቢዝነስዎ

Dec 26, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
124.6101 127.1023
GBP
153.1919 156.2557
EUR
135.1144 137.8167
AED
30.7026 31.3167
SAR
30.0597 30.6609
CHF
135.4765 138.1860

Exchange Rate
Close