የኢንቨስትመንት ቁጠባ ሂሳብ በየወሩ ቋሚ ገቢ ያላቸዉ ደንበኞች በየወሩ መደበኛ የቁጠባ መጠን ለሚቆጥቡት የተዘጋጀና ከፍተኛ የወለድ ምጣኔን የሚያስገኝ ሆኖ በወር አንዴ የሚቆጠብበት ከ1 ዓመት እስከ 10 ዓመት የሚቆይ የቁጠባ ሂሳብ ነዉ፡፡
የኢንቨስትመንት ቁጠባ ሂሳብ አጠቃቀም፡-
- ሂሳቡ በባንክ ደበተር ይንቀሳቀሳል፤
- የገንዘብ ተቀማጭነት የጊዜ ገደብ ከአንድ ዓመት እስከ አስር ዓመት ይሆናል፤
- የመነሻ ሂሳብ መክፈቻና ወርሃዊ ቁጠባ መጠን ለግለሰቦች 1,000.00 ብር ሲሆን ለድርጅቶች 3,000.00 ብር ነዉ፡፡
የኢንቨስትመንት ቁጠባ ሂሳብ ጠቀሜታዎች
- ሂሳቡ ከ5.5% እስከ 7.5% ከፍተኛ ወለድ ያስገኛል፤
- የቁጠባ ጊዜዉ ባደገበት ወቅት ባንኩ ከአጠቃላይ የገንዘቡ መጠን እስከ 60% የብድር አገልግሎት ያቀርባል፡፡
የኢንቨስትመንት ቁጠባ ሂሳብ ተጠቃሚዎች፡-
የኢንቨስትመንት ቁጠባ ሂሳብ የተዘጋጀዉ በቅጥር ለሚሰሩ ሠራተኞች፣ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፣ ለማህበራት፣ ለንግድ ማህበራትና ለመሳሰሉት ነዉ፡፡
የሚያስፈልጉዎት ቅጾች