የአዋሽ ባንክ አገልግሎቶች
ሀ) ልዩ የቁጠባ ሂሳብ
1.የቁጠባ ሂሳብ
የቁጠባ ሂሳብ የወለድ ምጣኔን የሚያስገኝ የባንኩን መመዘኛዎች የሚያሟሉ ግለሰቦች፣ ድርጅቶች፣ ማህበራትና የመሳሰሉት የሚጠቀሙበት ሂሳብ ነዉ፡፡
1.1 የቁጠባ ሂሳብ አጠቃቀም፡-
- የወለድ ምጣኔን ያስገኛል፤
- የባንኩን ዝቅተኛ መመዘኛዎች የሚያሟላ ማንኛዉም ሰዉ ሂሳቡን መክፈት ይችላል፤
- በባንክ ደብተር ወይም ያለ ባንክ ደብተር መጠቀም ያስችላል፡፡
1.2 የቁጠባ ሂሳብ ጠቀሜታዎች፡-
- ደንበኞች ገንዘባቸዉን በባንክ ለማስቀመጥ ያገለግላል፤
- ከተቆጠበዉ ገንዘብ ወለድ ያገኛሉ፡፡
1.3 ተጠቃሚዎች፡-
- ዕድሜያቸዉ ከ18 ዓመት በላይ የሆናቸዉ ሁሉ፡፡
1.4 ሂሳቡን ለመክፈት የሚያስፈልጉ ዶክመንቶች፡-
- በቅርብ የተነሱት ሁለት ፎቶግራፎች፤
- የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፤
- የታደሰ ፓስፖርት፤
- ዜግነትን የሚገልጽ መታወቂያ፤
- ግሪን ካርድ፤
- የቅጥር ወይም የመስሪያ ቤት መታወቂያ፤
- የዩኒቨርሲቲ መታወቂያ፤
- የመንጃ ፈቃድ እና የመሳሰሉት፡፡
2.ተንቀሳቃሽ ሂሳብ፡-
- ተንቀሳቃሽ ሂሳብ የወለድ ምጣኔ የማያስገኝ ሂሳብ ሲሆን ለተማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚያገለግል ነዉ፡፡
2.1 የተንቀሳቃሽ ሂሳብ አጠቃቀም፡-
- ወለድ አያስገኝም፤