የታታሪዎቹ ውድድር አሸናፊዎች ሽልማታቸውን ተረከቡ

ግንቦት 22 ቀን 2015 ዓ.ም አዋሽ ባንክ፣ በሀገራችን የሚሰተዋለውን የስራ አጥነት ችግርን በመፍታት ረገድ ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖረው የሚታመነው የ “ታታሪዎቹ” ፕሮጀክት ላይ በርካታ ወጣቶች በመሳተፍ የቢዝነስ ሙያ ስልጠና ተጠቃሚ ከመሆናቸውም በተጨማሪ ለተከታታይ ሳምንታት የቴሌቪዥን የስርጭት ሽፋን በነበረው የስራ ፈጠራ ሀሳብ ውድድር ላይም በናሙና (prototype) የተደገፈ ስራዎቻቸውን በማቅረብና ብርቱ ፉክክር በማድረግ በዳኞች ውሳኔ መሰረት ከ 1 – 5ኛ ደረጃዎች ውስጥ ለገቡ አሸናፊዎች ለእያንዳንዳቸው ማለትም ለ1ኛ ደረጃ አሸናፊ የብር 1 ሚሊዮን፣ 2ኛ ለወጣው አሸናፊ የብር 700 ሺህ፣ ለ3ኛ የብር 500 ሺህ፣ ለ4ኛ የብር 300 ሺህ እንዲሁም 5ኛ ደረጃ ላይ ለሚገኘው ተወዳዳሪ የብር 200 ሺህ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል እንዲሁም ከዋስትና ነፃ እስከ ብር 5 ሚሊዮን ብድር እንደየ ፕሮጀክታቸው ሁኔታ ተመቻችቶላቸዋል ፡፡
ባንኩ በስካይ ላይት ሆቴል ባካሄደው የታታሪዎቹ ውድድር የማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው እንደገለፁት የኮርፖሬት ማህበራዊ ሃላፊነት አካል የሆነው የታታሪዎቹ ፐሮጀክት ለወደፊቱም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅሰዋል፡፡ በሥነ ሥርዓቱ ላይ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችን ጨምሮ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

Jul 26, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
57.4895 58.6393
GBP
70.6759 72.0894
EUR
62.3359 63.5826
AED
14.1646 14.4479
SAR
13.8682 14.1456
CHF
62.5028 63.7529

Exchange Rate
Close