አዋሽ ባንክ የ2022/23 ዓመታዊ የሥራ አመራር ስብሰባ አካሄደ

አዋሽ ባንክ የ2022/23 ዓመታዊ የሥራ አመራር ስብሰባ ሐምሌ 28 እና 29 ቀን 2015 ዓ.ም በእስካይ ላይት ሆቴል አካሂዷል።

የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራዉ በጉባኤው የመክፈቻ ንግግር ላይ እንደ ገለፁት ባንኩ ባጠናቀቀዉ ሂሳብ ዓመት አመርቂ ውጤት ሊያስመዘግብ የቻለው ሊፍጠሩ የሚችሉ ተግዳሮቶችን ለመከላከል ያወጣውን እስትራቴጂ በአግባቡ በመከተልና በመተግበሩ ነው ብለዋል::

ባንኩ በተጠናቀቀዉ የሂሳብ ዓመት ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት የግል ባንኮች መካከል በሁሉም የባንኪንግ የስራ ዘርፎች የመሪነት ስፍራውን እንደያዘ የቀጠለ ሲሆን ይህንን ለማስቀጠል ባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል ከፍተኛ መዋለ ንዋይ ፈሰስ በማድረግና ዘርፉን በሚደግፍ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አክለዋል:: በመጨረሻም በተጠናቀቀዉ ሂሳብ ዓመት አመርቂ ውጤት ላስመዘገቡት ና የቀጠና ጽ/ቤቶች እና ቅርንጫፎች ዕውቅናና የማበረታቻ ሽልማት በማበርከት ስብሰባውን አጠናቋል::

May 30, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
57.0424 58.1832
GBP
69.4344 70.8231
EUR
61.8910 63.1288
AED
14.0526 14.3337
SAR
13.7637 14.0390
CHF
59.7647 60.9600

Exchange Rate
Close