አዋሽ ባንክ የስራ እድል ፈጠራን የሚያበረታታ የ ‘ታታሪዎቹ’/ ቀጠሌዋን የሁለተኛ ዙር ፕሮጀክት ይፋ አደረገ

አዋሽ ባንክ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አኳያ ስራ ፈጣሪዎችንና ወጣት ትውልድን ለማበረታታትና ተገቢውን የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችለውን ፕሮጀክት ቀርጾ ወደ ትግበራ መግባቱን ይፋ አድርጓል፡፡
በተካሄደው ሁለተኛው ዙር የ ‘ታታሪዎቹ’/ ቀጠሌዋን የስራ ፈጠራ ውድድር ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ላይ የባንኩ ዋና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው እንደገለፁት ስራ ፈጣሪ የሆኑ ዜጎቻችን በተለይም ወጣት ወንዶችና ሴት እህቶቻችን የእድሉ ተጠቃሚ በመሆን የቢዝነስ ሀሳባቸውን ዕውን በማድረግ በአገራቸው ዕድገት ላይ የራሳቸውን አሻራ እንዲያሳርፉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የተወዳዳሪ ስራ ፈጣሪዎች ከጥቅምት 12 እስከ ህዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም በበይነ መረብ (ኦን ላይን) ወይንም በሁሉም አዋሽ ባንክ ቅርንጯፎች በአካል በመገኘት ማመልከት እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡

Jul 23, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
57.4671 58.6164
GBP
70.9941 72.4140
EUR
62.5644 63.8157
AED
14.1591 14.4423
SAR
13.8651 14.1424
CHF
61.8239 63.0604

Exchange Rate
Close