አዋሽ ባንክ እና አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ አረንገጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

የእህት ኩባንያዎቹ አዋሽ ባንክ እና አዋሽ ኢንሹራንስ ሠራተኞች በዛሬው እለት ሐምሌ 01 ቀን 2015 ዓ.ም ለአምስተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከቦሌ ክፍለ ከተማ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በአይሲቲ ፓርክ 20 ሺህ ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

እህት ኩባንያዎቹ በኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊነት መርሐ ግብራቸው በስፋት ከሚሳተፉባቸው ተግባራት አንዱ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን መደገፍ ሲሆን በተለይ ባለፉት 29 ዓመታት ውስጥ በሀገራችን የልማትና የምጣኔ ሀብት ዕድገት ውስጥ አሻራቸውን ካስቀመጡት የግል የፋይናንስ ተቋማት መካከል ግንባር ቀደም መሆናቸው ይታወቃል፡፡

Jul 26, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
57.4895 58.6393
GBP
70.6759 72.0894
EUR
62.3359 63.5826
AED
14.1646 14.4479
SAR
13.8682 14.1456
CHF
62.5028 63.7529

Exchange Rate
Close