አዋሽ ባንክ አዲስ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ ይፋ አደረገ

ነሐሴ 16/2015 (አዋሽ ባንክ) አዋሽ ባንክ እና አምሪፍ ኸልዝ ጋር በመተባበር በብድርና ቁጠባ ዘርፍ የበለፀገ አዲስ የፋይናንስ ቴክኖሎጂን ይፋ አድርጓል፡፡
“ሳኮስ ኮርፖሬት ቢዝነስ ሶልዩሽን” የተሰኘው ቴክኖሎጂ አነስተኛ እና መሰረታዊ የባንክ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ቴክኖሎጂው የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበራትን አገልግሎት ቀልጣፋ ለማድረግ፣ ተደራሽነታቸውን ለማጎልበት፣ ብሎም በዘርፉ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው የአዋሽ ባንክ ሲኒየር ቺፍ ሪቴይል ኤንድ ኤስ.ኤም.ኢ ባንኪንግ ኦፊሰር በአቶ ሄኖክ ተሰማ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ገልጸዋል፡፡
ባንኩ ዛሬ ያስተዋወቀው የፋይናንስ ቴክኖሎጂ ለከፍታ የተቀናጀ የወጣቶች ፕሮጀክት የብድርና ቁጠባው ዘርፍ በነፃ ያቀረበ ሲሆን በዚህ አዲስ ቴክኖሎጂ የአባላት ምዝገባና አያያዝ፣ የብድር አገልግሎት አስተዳደር፣ አክሲዮን እና የአክሲዮን ድርሻ ክፍያን ጨምሮ ሌሎች በርካታ አገልግሎቶች ይሰጣል ተብሏል።

Nov 28, 2023 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
55.6854 56.7991
GBP
67.1870 68.5307
EUR
60.9588 62.1780
AED
13.7216 13.9960
SAR
13.4363 13.7050
CHF
60.3764 61.5839

Exchange Rate
Close