አዋሽ ባንክ በባሌ ሮቤ ከተማ ያስገነባውን ህንፃ አስመረቀ

በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች የራሱን ህንፃ በመገንባት የሚታወቀው አዋሽ ባንክ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በባሌ ዞን በሮቤ ከተማ ያስገነባውን ባለ 4 ወለል ዘመናዊ ሕንጻ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች በተገኙበት በድምቀት በማስመረቅ ለአገልግሎት አብቅቷል፡፡
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ባላቸው የቱሪስት መስህቦችና በምርታማነቱ በሚታወቀው የባሌ ዞን መዲና በሆነችው የሮቤ ከተማ የተገነባው ይህ ህንጻ የተገነባበት አካባቢ ለንግድና ለተለያዩ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ተፈላጊ ሥፍራ በመሆኑ ለሀገሪቱ ብሎም ለክልሉ ያለው የኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

Jul 26, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
57.4895 58.6393
GBP
70.6759 72.0894
EUR
62.3359 63.5826
AED
14.1646 14.4479
SAR
13.8682 14.1456
CHF
62.5028 63.7529

Exchange Rate
Close