አዋሽ ባንክ የ1444ኛውን የረመዳን ጾምን በማስመልከት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም ምኞቱን ለመግለጽና ለደንበኞቹ ያለውን አጋርነት ለማረጋገጥ በማሰብ በዛሬው እለት በሸራተን አዲስ ሆቴል የጋራ የኢፍጣር ሥነ-ሥርዓት አካሂዷል፡፡
በመርሐ-ግብሩ ላይ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራውን ጨምሮ ፣ የአዋሽ ባንክ የሸሪዓ አማካሪዎች ፣ የባንኩ የሥራ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፣ ባንኩ በሸሪዓ መርሆች ላይ የተመሰረተውን የአዋሽ ኢኽላስ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ዓይነቶችና ተደራሽነት ለማስፋት ጠንክሮ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።









