እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!

አዋሽ ባንክ ከዓለም ምርጥ ባንኮች ውስጥ አንዱ ሆኖ ለሶስተኛ ጊዜ ተመረጠ!

ግሎባል ፋይናንስ መጋዚን ለ31ኛ ጊዜ ዓመታዊ የዓለም እና የየአገሮች ምርጥ ባንኮችን ምርጫን ይፋ ባደረገው መሠረት በምርጫው ከተካተቱት 36 የአፍሪካ ሃገራት ውስጥ ከተመረጡት ምርጥ የአፍሪካ ባንኮች መካከል አዋሽ ባንክ ከኢትዮጵያ ምርጥ ባንክ በመሆን ለ3ኛ ጊዜ ተመረጠ፡፡
እ.ኤ.አ. በ2024 ዓ.ም የተካሄደው ምርጫ ከ150 በላይ ባሉ አገራት የሚሠሩ ባንኮች የተካተቱበት ሲሆን የምርጫው ዋና ዋና መስፈርቶች የሚለኩና /quantitative objective/ በመረጃ ላይ የተደገፉ የማይለኩ /informed subjective/ መሥፈርቶችን ያካተተ ነው።
ለአሸናፊ ባንኮች የሚሰጠው ዕውቅናና ሽልማት ስነስርአትም የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና የዓለም ባንክ (WB) በዋሽንግተን ዲሲ እ.ኤ.አ. በኦክቶበር 2024 በሚያደርጉት የጋራ ጉባዔ ላይ እንደሚከናወን ታውቋል፡፡
ይህ የእውቅና ሽልማት የተገኘው ክቡራን ደንበኞቻችን በባንካችን ላይ ባላችሁ እምነት እና ከኛ ጋር ስለሰራችሁ ስለሆነ በዚሁ አጋጣሚ ለውድ ደንበኞቻችን የላቀ ምስጋናችንን እያቀረብን ለወደፊቱም በበለጠ ደረጃ ልናገለግላችሁ ዝግጁ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡
አዋሽ ባንክ!

Dec 21, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
124.6101 127.1023
GBP
153.1919 156.2557
EUR
135.1144 137.8167
AED
30.7026 31.3167
SAR
30.0597 30.6609
CHF
135.4765 138.1860

Exchange Rate
Close