አዋሽ ባንክ ‘’ለላቀ የደንበኞች እርካታ እንተጋለን’’ በሚል መሪ ቃል በሁሉም ቅርንጫፎቹ ውስጥ ከዛሬ ሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ በዓይነቱ ለየት ያለ የደንበኞች ሳምንትን እያከበረ ይገኛል፡፡ በደንበኞች ሳምንት የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው በቅርንጫፎች ላይ በመገኘት ለተለያዩ ደንበኞች የባንክ አገልግሎት ሰጥተዋል፡፡.