News

አዋሽ ባንክ ከያንጎ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

በስምምነቱ መሰረት ሁሉም የአዋሽ ባንክ ደንበኞች የያንጎ የሞባይል መተግበሪያን ተጠቅመው የጉዞ ጥሪ ሲያደርጉ Awash00 ፕሮሞ ኮድ በመጠቀም እና የክፍያ አማራጫቸውን አዋሽ ባንክ በማድረግ በአዋሽብር ፕሮ ክፍያቸውን ሲፈጽሙ፣ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ጉዞዎች ላይ የ15% ቅናሽ የሚያገኙ መሆኑ ተጠቁሟል።አዋሽ ባንክ ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር የመግባቢያ ስምምነት በማድረግ በትብብር በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

የታታሪዎቹ/ቀጠሌወን ውድድር የቴሌቪዥን ፕሮግራም ጥቆማ!

በጉጉት የሚጠበቀው የአዋሽ ባንክ ታታሪዎቹ/ቀጠሌወን የስራ ፈጠራ ውድድር ተወዳዳሪዎች የፈጠራ ሀሳቦቻቸውን የሚያቀርቡበትና የሚፋለሙበት መሰናዶ እሁድ ጥቅምት 24 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በፋና ቴሌቪዥን እንዲሁም በተመሳሳይ ቀን ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በOBN ቴሌቪዥን መተላለፍ ይጀምራል። እንዳያመልጥዎ!አዋሽ ባንክ!

እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!

ግሎባል ፋይናንስ መጋዚን ለ31ኛ ጊዜ ዓመታዊ የዓለም እና የየአገሮች ምርጥ ባንኮች ምርጫን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ በምርጫው ከተካተቱት 36 የአፍሪካ ሃገራት ውስጥ ከተመረጡት ባንኮች መካከል አዋሽ ባንክ ከኢትዮጵያ ብቸኛው ምርጥ ባንክ በመሆን በተከታታይ ለ3ኛ ጊዜ መመረጡ የሚታወስ ሲሆን፣ የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና የዓለም ባንክ (WB) በዋሽንግተን ዲሲ ባደረጉት የጋራ ጉባኤ ላይ የዕውቅና ሽልማቱን የባንካችን ዋና […]

አዋሽ ባንክ ታማኝ የግብር ከፋይ ሽልማት ተበረከተለት

የ6ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና እና ሽልማት ሥነ-ሥርዓት በትናንትናው እለት በብሔራዊ ቤተ-መንግስት በተካሄደበት ወቅት ባንካችን ከፍተኛ ግብር በታማኝነት በመክፈሉ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእዉቅና ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡በፋይናንስ ዘርፉ ፈር ቀዳጅ የሆነውና 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በማክበር ላይ የሚገኘው አዋሽ ባንክ የአገልግሎት አድማሱን ከማስፋቱም ባሻገር የወገኖቻችንን ህይወት ለማሻሻል የሚረዱ ተግባራትን በሃላፊነት መንፈስ […]

አዋሽ ባንክና አዋሽ ኢንሹራንስ 30ኛ ዓመት የምሥረታ በዓላቸውን ማክበር ጀመሩ

እህት ኩባንያዎቹ አዋሽ ባንክና አዋሽ ኢንሹራንስ አ/ማ በተለያዩ መርኃ-ግብሮች የሚከበረውን የ30ኛ ዓመት የምስረታ በዓላቸውን የማብሰሪያ ስነ-ስርዓት በዛሬው ዕለት በዋናው መ/ቤታቸው በፌደራል ፖሊስ ማርሽ ባንድ ሙዚቃ በመታጀብ በዓሉን በይፋ አስጀምረዋል፡፡በዛሬው ዕለት በይፋ የተጀመረው የእህት ኩባንያዎቹ የ30ኛ ዓመት ክብረ- በዓል በየቀጠና ጽ/ቤቶቻቸው እና በየቅርንጫፎቻቸው በተከታታይ ለሶስት ወራት በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ይሆናል፡፡

Page 2 of 12
1 2 3 4 12

Dec 21, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
124.6101 127.1023
GBP
153.1919 156.2557
EUR
135.1144 137.8167
AED
30.7026 31.3167
SAR
30.0597 30.6609
CHF
135.4765 138.1860

Exchange Rate
Close