አዋሽ ባንክ የሥራ ፈጣራ ክህሎትን ለማበረታታት ጠንክሮ እንደሚሰራ ገለጸ

የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው የማጠቃለያ መርሐ-ግብሩ ላይ እንዳሉት፣ ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አኳያ ስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታትና ተገቢውን የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ አስቦ ታታሪዎቹ እና “ቀጠሌወን” የተሰኘ የስራ ፈጠራ ውድድር ማዘጋጀቱን ገልፀው፣ ባንካችን ለሀገር ሊጠቅሙ የሚችሉ አዳዲስ የስራ ፈጠራ ሃሳቦችን ይዘው ካለባቸው የፋይናንስ ችግር ግን ሀሳባቸውን እውን ለማድረግ ያልቻሉ ስራ ፈጣሪዎች አስፈለጊውን የፋይናንስ ድጋፍና የክህሎት ስልጠና መሰጠቱን ተናግሯል፡፡

በዚህም የስራ ፈጠራ ውድድር ላይ አዳዲስ እና ችግር ፈቺ የሆኑ የስራ ሀሳቦች ያላቸው ከሁሉም የአገራችን አካባቢዎች የተሳተፉበት ሲሆን የውድድሩ አሸናፊዎችም እንደየደረጃቸው ከብር አንድ መቶ ሺ እስከ አንድ ሚሊዮን እንደተሸለሙ እና ከዋስትና ነፃ እስከ ብር 5 ሚሊዮን ብድር እንደየፕሮጀክታቸው ሁኔታ የሚመቻችላቸው መሆኑንም ገልጿል፡፡ 

የእለቱ የክብር እንግዳ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ም/ል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አወሉ አብዲ በበኩላቸው አዋሽ ባንክ ለአንድ ዓመት ሲያካሄዱ የነበረውን በ“ቀጠሌወን” የሥራ ፈጠራ ውድድር የማጠቃላይ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ለአሸናፊዎች የምስክር ወረቀትና ባንኩ ያዘጋጀው የገንዘብ ሽልማት ቼክ ሰጥተዋል፡፡

አቶ አወሉ በሽልማት ስነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር አዋሽ ባንክ በባለቤትነት የሥራ ፈጠራ ክዕሎት ያላቸውን ወጣቶች ለማበረታታትና የሥራ ዕድል ለመፍጠር በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጥር በጀት በመመደብ እያደረገ ሲላለው የማህበራዊ ኃላፊነት ግዴታ ባንኩን አመሰገነዋል፡፡

ባንኩ ለብዙ ዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር የሥር ፈጠራ ክህሎትን ማበረታታቱ ለሌሎች መሰል ተቋማት ትልቅ ዓርአያ እየሆነ ስለሆነ የክልሉ መንግስት አሰፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ከባንኩ ጋር የሚቆምና እገዛ የሚያደርግ መሆኑን ቃል ገብቷል።

ከዚህም በተጨማሪ በዕለቱ ለተሸለሙ ተወዳዳሪ ወጣቶች የፈጠራ ሃሳባቸውን ወደ ምርትና ተግባር የሚለውጡ ከሆነ የክልሉ መንግስት የማምረቻና መሸጫ ቦታ ለአሸናፊዎቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል። 

አዋሽ ባንክ በአርቆ አሳቢና ራዕይ ባላቸው ሰዎች የተቋቋመ ባንክ በመሆኑ በሀገራችን ካሉት የግል ባንኮች መካከል ጠንካራና በጽኑ መሠረት ላይ የተገነባ ከኢትዮዽያ ንግድ ባንክ ቀጥሎ የሀገርቷ ግዙፍ የፋይናንስ ተቋም መሆኑን ጠቁመው በሀገራችን ኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ የራሱን አሻራ ያኖረ መሆኑን አመልክተዋል።

የወድድሩ አሸናፊዎችን በመወከል በሥነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረገው ወጣት ፀጋዬ ተስፋዬ ገና ካሁኑ የቀጠሌወን ማህበር መቋቋማቸውን አመልክተው ባንኩ ለአንድ ዓመት ያህል የውድድር መርሃ-ግብር በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ መዋለ ንዋይ በመመደብ ለውድድሩ አሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማትና ያለንብረት መያዥ ብድር ለመስጠት በመወሰኑ በማመስገን፣ ጠንክሮ በመስራትም የተሰጣቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ ገልጿል።   

ለፕሮግራሙ መሳካት ድጋፍ ላደረጉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።

Mar 29, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
56.6236 57.7561
GBP
68.3299 69.6965
EUR
61.1818 62.4054
AED
13.9527 14.2318
SAR
13.6630 13.9363
CHF
59.8379 61.0347

Exchange Rate
Close