አዋሽ ባንክ የመጀመርያው ግማሽ  ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ  አካሄደ።

አዋሽ ባንክ  እ.ኤ.አ. የ2022/23 በጀት አመት የመጀመርያው ግማሽ አመት የስራ አፍፃፀም ግምገማ  ጥር 28 ቀን 2015 ዓ.ም   ስካይላይት ሆቴል አካሂዷል። የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ያለፉት ስድስት ወራት  አጠቃላይ የባንኩ የስራ አፈጻጸም ከዕቅዱ አንፃር ሲታይ በሁሉም መለኪያዎች አበረታች መሆኑን ገልጸዋል። በበጀት ዓመቱ የመጀመርያው ግማሽ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ቅርንጫፎችና ቀጠና ጽ/ ቤቶች የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን  ጠንካራ አፈጻጸሙን ለማስቀጠል በአፈፃፀም ላይ  የተስተዋለሉ ክፍተቶችን በማሻሻል ባንኩን በኢንዱስትሪው ውስጥ ባለው መሪነት ለማስቀጠልም ከምግባባት ተደርሷል፡፡

በመጨረሻም የአዋሽ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አምባሳደር ዶክተር ዲባባ አብደታ ባሰተላለፉት መልዕክት የባንኩ የስራ አመራሮችና አጠቃላይ ሰራተኞች  በአዲሱ ስትራቴጂ ላይ የተቀመጠውን የባንኩን  ራዕይ ማለትም እ.አ.አ በ2027 ከሶስት የምስራቅ አፍሪካ ምርጥ ባንኮች አንዱ እና እ.አ.አ በ2030 ከአፍሪካ 10 ምርጥ  ባንኮች መካከል አንዱ መሆን የሚለዉን ለማሳካት ስራቸውን በብቃትና በጥበብ እንዲሰሩ  አሳስበዋል።

Apr 19, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
56.8204 57.9568
GBP
67.6774 69.0309
EUR
60.6615 61.8747
AED
13.9997 14.2797
SAR
13.7079 13.9821
CHF
59.7024 60.8964

Exchange Rate
Close