አዋሽ ባንክ በዓለም አቀፍ ማስተር ካርድ ለደንበኞች ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማቅረብ እና በማስጠቀም ላስመዘገበው የላቀ አፈፃፀም ከማስተር ካርድ (Mastercard) ከፍተኛ እውቅና አግኝቷል።
የማስተር ካርድ ሲኒየር ቫይስ ፕሬዝዳንት ካንትሪ ማናጀር ምስራቅ አፍሪካ እና ኢንዲያን ኦሽን ሽሪያር አሊ የሚመራዉ ልዑካን በዋና መስሪያ ቤታችን በመገኘት ሽልማቱን ለአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው አበርክተዋል።
በዕለቱም ከባንኩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በዲጂታል ባንኪንግ እና በስትራቴጂካዊ አጋርነት ላይ ፍሬያማ ውይይት ተደርጓል።
በየወሩ ከ4 ሚሊዮን ዶላር በላይ ግብይት በማስተናገድ ግንባር ቀደም የሆነው አዋሽ ባንክ፣ የደንበኞቹን የባንክ አገልግሎት ተሞክሮ ይበልጥ ለማዘመን በትጋት መስራቱን ይቀጥላል።

















