ባንካችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባዘጋጀው የፋይናንስ ፎረም ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል

ከዛሬ ግንቦት 07- 08 ቀን 2017 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት ለሚቆየውና በኢትዮጵያ የሳይናንስ ሙዚየም ውስጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባዘጋጀው የፋይናንስ ፎረም ላይ ባንካችን አዋሽ እየተሳተፈ ሲሆን በፎረሙም ላይ የኢፌዲሪ ፕሬዚደንት ክቡር ታዬ አስቀ ሥላሴ እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ በርካታ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ሀገር በቀል እና ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት፣ ፊንቴክ ድርጅቶች፣ የልማት አጋሮች እንዲሁም የግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

መርሐ-ግብሩ ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኘው አዋሽ ባንክም ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ የሚያደርጉ የባንክ አገልግሎቶችን ለተሳታፊዎችና ለጎብኚዎች በማስተዋወቅ ላይ ስለሚገኝ መጥተው እንዲጎበኙን እንጋብዝዎታለን::
አዋሽ ባንክ!

[rates_widgest title="EXCHANGE Rate" selected_currencies="USD, GBP, EUR, AED, SAR, CNY,JPY,CHF" more_link="#"]