አዋሽ ባንክ የመጋዘን ደረሰኝ የብድር አገልግሎት መስጠት ጀመረ!

የመጋዘን ደረሰኝ ብድር አንድ አምራች ወይም ተገበያይ ምርቱን ወደ ኢትዮጵያ ምርት ገበያ መጋዘን በማስገባትና የመጋዘን ደረሰኙን (WR) እንደ ማስያዣ በመጠቀም ከምርት ገበያው ጋር በጣምራ ከሚሰሩ ባንኮች ብድር አገልግሎት የሚያገኝበት አሰራር ነው፡፡በዚህ መሰረት ተበዳሪው አርሶ አደር፣ የህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየኖች እና አቅራቢዎች መያዣ እንዲሆን ካስገባው ምርት ውጭ ሌላ ንብረት ለመያዣነት ሳያስፈልገው ከባንክ የአጭር ጊዜ የብድር አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡
በዚሁ መሰረት አዋሽ ባንክ ከኢትዮጵያ የምርት ገበያ ድርጅት ጋር በመተባበር ለድርጅቱ ደንበኞች የአጭር ጊዜ ብድር አገልግሎት አቅርቧል፡፡ አዋሽ ባንክ ይህንን የብድር አገልግሎት የሚሰጠው በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት እንዲገበያዩና በድርጅቱ መጋዘኖች እንዲከማቹ ለተፈቀደ የግብርና ግብዓቶች ሲሆን የብድር አገልግሎቱን ለማግኝት አምራቾቹ ባንኩ በብድር ፖሊሲው ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች አሟልተው መገኘት አለባቸው፡፡
Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Apr 18, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
56.8022 57.9382
GBP
67.5744 68.9259
EUR
60.4375 61.6463
AED
13.9956 14.2755
SAR
13.7039 13.9780
CHF
59.5391 60.7299

Exchange Rate
Close