እህት ኩባንያዎቹ አዋሽ ባንክና አዋሽ ኢንሹራንስ አ/ማ በተለያዩ መርኃ-ግብሮች የሚከበረውን የ30ኛ ዓመት የምስረታ በዓላቸውን የማብሰሪያ ስነ-ስርዓት በዛሬው ዕለት በዋናው መ/ቤታቸው በፌደራል ፖሊስ ማርሽ ባንድ ሙዚቃ በመታጀብ በዓሉን በይፋ አስጀምረዋል፡፡
በዛሬው ዕለት በይፋ የተጀመረው የእህት ኩባንያዎቹ የ30ኛ ዓመት ክብረ- በዓል በየቀጠና ጽ/ቤቶቻቸው እና በየቅርንጫፎቻቸው በተከታታይ ለሶስት ወራት በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ይሆናል፡፡