አዋሽ ባንክ በዛሬው እለት በስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደው የስታር ዋይድ አዋርድ የሽልማት መርሃ ግብር ላይ በዓመቱ በባንክ ዘርፍ ‘’እጅግ ከፍተኛ አፈፃፀም’’ ያሳየ ባንክ በመሆን ሽልማት የተበረከተለት ሲሆን ምርጫውም በህዝብ ድምፅ መሰረት የተከናወነ ነበር፡፡
ይህ የእውቅና ሽልማት የተገኘው ክቡራን ደንበኞቻችን በባንካችን ላይ ባላችሁ እምነት እና ከኛ ጋር ስለሰራችሁ በመሆኑ በዚሁ አጋጣሚ የላቀ ምስጋናችንን እያቀረብን ለወደፊቱም በበለጠ ልናገለግላችሁ ዝግጁ መሆናችንን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
አዋሽ ባንክ!



















