ግሎባልፋይናንስ አዋሽ ባንክን ለ4ተኛ ጊዜ በአፍሪካ ምርጥ ባንኮች አንዱ እና ከኢትዮጵያ ብቸኛ ባንክ አድርጎ መረጠ::
ግሎባል ፋይናንስ መፅሄት እ.ኤ.አ. በማርች 2025 ለ32ኛ ጊዜ የምርጥ ባንኮችን ምርጫ ይፋ ማድረጉን አስመልክቶ ለአዋሽ ባንክ በላከው መልዕክት አዋሽ ባንክ ከአፍሪካ ዉስጥ ምርጥ ባንኮች ተብለዉ ከተመረጡ 36 ባንኮች መካከል አንዱ ሆኖ በተከታታይ ለ4ኛ ጊዜ መመረጡንና ከኢትዮጵያ ደግሞ ብቸኛ ባንክ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡
ለአሸናፊባንኮች የሚሰጠው ዕውቅናና ሽልማት ስነስርአትም የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና የዓለም ባንክ (WB) በዋሽንግተን ዲሲ እ.ኤ.አ. በኦክቶበር 2025 በሚያደርጉት የጋራ ጉባዔ ላይ እንደሚከናወን ታውቋል፡፡
ይህየእውቅና ሽልማት የተገኘው ክቡራን ደንበኞቻችን በባንካችን ላይ ባላችሁ ከፍተኛ እምነት ስለሆነ በዚሁ አጋጣሚ ለውድ ደንበኞቻችንየላቀ ምስጋናችንን እያቀረብን ለወደፊቱም በበለጠ ልናገለግላችሁ ዝግጁ መሆናችንን በዚሁ አጋጣሚ እንገልፃለን፡፡



















