የማስጀመሪያ ስነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዋሽ ካፒታል አ.ማ. የቦርድ ሰብሳቢ እና የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው በተናገሩት መሰረት ሀገራችን በፋይናንስ ዘርፍ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አዲስ ምዕራፍ በመግባት ዘርፈ ብዙ ለውጦችን እያደረገች በምትገኝበት በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን መቋቋሙ ለቢዝነስ ዘርፉ ትልቅ መነቃቃትን እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡
የአዋሽ ባንክ ተቀጥላ ኩባንያ የሆነው አዋሽ ካፒታል አ.ማ ህጉ የሚጠይቃቸውን መስፈርቶችና መመዘኛዎች በተገቢው ሁኔታ በሟሟላት ሙሉ የኢንቨስትመንት ባንክ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ፈቃድ ህዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን መቀበሉን አሳውቀዋል፡፡ በማከልም አዋሽ ካፒታል እ.ማ ለሀገራዊ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት በተገቢው ሁኔታ ራሱን በማደራጀት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የዝግጅት ምዕራፉን በማጠናቀቅ በሁለት መቶ ሚሊዮን ካፒታል ስራ መጀመሩ ተገልጿል፡፡



















