አዋሽ ባንክ 22ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን አከበረ

አዋሽ ባንክ 22ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ትውልድን በሥነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሠራር!” በሚል መሪ ሃሳብ ለባንኩ ከፍተኛ የስራ አመራር የግንዛቤ ማስጨበጫ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል አካሄዷል፡፡
መርሐ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የባንኩ ሲኒየር ቺፍ ሆልሴል ባንኪንግ ኦፊሰር እና የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ ታደሰ ገመዳ እንደገለፁት ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የትዉልድ ሥነ ምግባር ግንባታ ማጠናከር እንደሚገባ በመግለፅ መሰል የምክክር መድረኮች መኖራቸው በተለይ ሰራተኞች በስነ-ምግባር ታንፀው ሙያዊ የሥራ ዲሲፒሊን በመላበስ የማገልገል ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው አመላክተዋል፡፡
በመጨረሻም የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የሀብት ማሳወቂያ የምዝገባ ሰነድ ርክክብ በማድረግ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

Mar 12, 2026 - EXCHANGE Rate
CurrencyCash and Remittances through AgentsTransaction
BuyingSellingBuyingSelling