አዋሽ ባንክ የ2017 ዓ.ም የፋሲካ በዓልን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ እየሱስ ፕሬዝዳንት ክቡር ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ ፣ የሀይማኖት አባቶች እና በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በዛሬው እለት በመካኒሳ መካነእየሱስ ሴምናሪ ውስጥ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።
በስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው እንደገለፁት መጪውን የ2017 ዓ.ም የፋሲካ በዓልን በማስመልከት ቀደም ሲል አዲስ አበባን ጨምሮ በመላዉ ሀገሪቱ ከአንድ መቶ በላይ በሚሆኑ የድጋፍ መስጫ ጣቢያዎች ከአስር ሺህ በላይ ለሚሆኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ፣ ጧሪ ለሌላቸዉ አረጋውያን እና ሌሎች ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ከ63 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለበዓሉ የዓይነት እና የገንዘብ ድጋፍ መደረጉን ጠቁመው በቀጣይም ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እያከናወነ በሚገኘው የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነእየሱስ ፕሬዝዳንት ክቡር ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ በበኩላቸው አዋሽ ባንክ እያደረገ ላለው በጎ ተግባር ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡



















