አዋሽ ባንክ “ለላቀ የደንበኞች እርካታ እንተጋለን’’ በሚል መሪ ቃል ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የደንበኞች ሳምንት ከዛሬ የካቲት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በዋናው መስሪያ ቤት እና በሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች በደማቅ ሁኔታ ማክበር ጀምሯል፡፡
የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው በመርሃ-ግበሩ ማስጀመሪያ ስነ-ሥርዓት ላይ እንደገለጹት ባንኩ ከምስረታው ጊዜ ጀምሮ የደንበኞቹን ፍላጐት ለማርካት ደንበኞችን ማዕከል ያደረጉ ደንበኛ-ተኮር አገልግሎቶችን እያቀረበ ሰላሳ አንድ ዓመታትን በስኬት መጓዙን ገልፀዋል።
ባንኩ ለደንበኞች ተደራሽነቱን ለማስፋት የቅርንጫፎቹን ብዛት ከ1000 በላይ ያደረሰ ሲሆን፣ በተጨማሪም በዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ዘርፍ ሰፊ ስራ እየሰራ ይገኛል። ከዚህም ባሻገር በባንኩ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ባለፉት 6 ወራት የተከናወነዉ የክፍያ መጠንም አንድ ትሪሊየን ብር መድረሱ ተገልጿል፡፡
አዋሽ ባንክ



















