አዋሽ ባንክ ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ሊያጋጥም የሚችለውን የንግድ ሂደት መስተጓጎል ከግምት በማስገባት የሚከተሉትን የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያዎችን አድርጓል፡፡

1. ከውጪ አገር ምርቶችን የሚያስገቡ ደንበኞቻችን ለኤልሲ ማራዘሚያ ይከፍሉ የነበረው ኮሚሽን ሙሉ በሙሉ ተነስቷል ፡፡
2. የብድር መመለሻ የመክፈያ ጊዜ ደንበኞቻችን እንዲራዘምላቸው ለሚያቀርቡት ጥያቄ ይከፈል የነበረው ኮሚሽን ሙሉ በሙሉ ተነስቷል ፡፡
3. ደንበኞቻችን ከኤቲኤም ገንዘብ ሲያወጡ ይከፍሉ የነበረውን የኮሚሽን ክፍያ ተነስቶ ነጻ ሆኗል ፡፡

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Loading exchange rates...