አዋሽ ባንክ ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ጋር አብሮ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

አዋሽ ባንክ ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ጋር በቀጣይ ጊዜያት በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን፣ በስምምነቱም መሰረት ባንካችን በተለያዩ የፕሮጀክት ፋይናንሲንግ እና በሰራተኞች የብድር አቅርቦት ላይ አብሮ መስራት ያሚያስችል ነው።
አዋሽ ባንክ ቀደም ሲል ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ የልማት ተቋማት ጋር ለመስራት የሚያስችሉትን የመግባቢያ ሰምምነቶችን በመፈራረም ተቋማቱ የሚፈልጉትን የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
አዋሽ ባንክ!

Mar 12, 2026 - EXCHANGE Rate
CurrencyCash and Remittances through AgentsTransaction
BuyingSellingBuyingSelling