አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23 ቀን 2018
አዋሽ ባንክ የ2018 የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከታሚሶል ኮሚዩኒኬሽን ጋር በመተባበር በዓይነቱ ልዩ የሆነ የአዋሽ ብር ፕሮ፣ ፋሲካ ኤክስፖ 2018 የመክፈቻ ስነ-ሥርዓት ዛሬ መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል አካሂዷል፡፡
ይህ አዋሽ ብር ፕሮ፣ ፋሲካ ኤክስፖ 2018 የንግድ ትርዕትና ባዛር በአዋሽ ባንክ የታይትል ስፖንሰርነት የተዘጋጀ እና ለሁለት ሳምንታት የሚካሄድ ኤክስፖ ነው። በዚህ የንግድ ትርዕትና ባዛር ከፍተኛ መጠን ያለው ተሳታፊ ኤክስፖውን ይጎበኛል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ሻጮችንና ሸማቾችን በአንድ ስፍራ በማገናኘት የበዓል ገበያውን የደመቀ ያደርገዋል፡፡
አዋሽ ባንክ በዚህ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ሁነት ላይ ሸማቾች በቀላሉ መገበያየት ያስችላቸው ዘንድ በአንድ ማዕከል የተሟላ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል አሰራር አመቻችቷል፡፡ በተጨማሪም ባንኩ የኤስፖው ተሳታፊዎች በንቃት በመሳተፍና ባመቻቸላችው የተለያዩ አማራጮች በመገበያየት ጊዜያቸውን በደስታ እንዲያሳልፉ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
በዚህ ኤክስፖ ላይ አዋሽ ኢ-ቲኬቲንግ የሚባል አዲስ የዲጂታል መተግበሪያ በተግባር ላይ ውሎ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ይህ አዲስ የዲጂታል መተግበሪያ ኮንሰርቶችን ጨምሮ ማንኛውንም ሁነት የሚያዘጋጁ አካላት ትኬቶችን ሙሉ በሙሉ በኦን-ላይን እንዲሸጡ እና እንዲያስተዳድሩ የሚያስችል ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያ ነው። መተግበሪያው የወረቀት ትኬቶችን በኪው.አር. ኮዶች (QR Codes) በመተካት ለአዘጋጆች እና ለታዳሚዎች ምቹ የሆነ አገልግሎት የሚሰጥ ነዉ።
በተጨማሪም በአዋሽ ብር ፕሮ ፋሲካ ኤክስፖ 2018 ላይ ሸማቾች ዘመኑን የዋጀ እና የዲጂታል ትሩፋት በሆነው በአዋሽ ኢ-ቲኬቲንግ ለሚጠቀሙ የንግድ ትርዕቱና የባዛሩ ታዳሚዎች አውቶሞቢል እና ሌሎች አጓጊ ሽልማቶች የሚያገኙበት ዕድሎችን ያዘጋጀ በመሆኑ በመተግበሪያው እንዲጠቀሙ ይጋብዛል፡፡ ከዚህም ባሻገር ባንኩ በአዋሽ ብር ፕሮ ግብይታቸውን ለሚፈጽሙ ሸማቾች 5% ተመላሽ የሚያገኙበት ዕድል አመቻችቷል።



















