አዋሽ ባንክ ከማስያዣ ነፃ የብድር አገልግሎት ለጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች መስጠት እንደሚጀምር አስታወቀ::

አዋሽ ባንክ በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን እና ለጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሆን ያለ ማስያዣ ከኢንሹራንስ ጋር የተጣመረ የዲጂታል የብድር አገልግሎት በቅርቡ ሊጀምር እንደሆነ አስታወቀ፡፡ የዲጂታል መተግበሪያው ኢንተርፕራይዞች አስፈላጊውን ብድር እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን በተመሳሳይ ጊዜ ብድር የመክፈል አቅማቸውን ሊያደናቅፉ ከሚችሉ ያልተጠበቁ ስጋቶች እንደሚጠብቃቸው እና ዘላቂ የሆነ የፋይናንስ አገልግሎት እንደሚሰጥ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሃይ ሽፈራው አስታውቀዋል፡፡ ባንኩ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ቢዝነሶችን ከፍ ለማድረግ ያስችል ዘንድ በሂሳብ እንቅስቃሴያቸው ላይ ብቻ የተመሰረተ ብድር ለመጀመር ሁሉንም አስፈላጊ ሂደቶችን ማጠናቀቁን እና በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገባ ያስታወቁት ዋና ስራ አስፈጻሚው መተግበሪያውን ተግባራዊ ለማድረግ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Mar 12, 2026 - EXCHANGE Rate
CurrencyCash and Remittances through AgentsTransaction
BuyingSellingBuyingSelling