አዋሽ ባንክ እ.ኤ.አ. በ2024/25 የሂሣብ ዓመት ከ22 ቢሊዮን ብር በላይ ዓመታዊ ትርፍ አስመዘገበ

ባንኩ በሂሳብ ዓመቱ በሃገራችን የተወሰዱ የማይክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ታሣቢ ያደረገ የስትራቴጂ ክለሳ በማድረግ በሁሉም ዋና ዋና የባንክ የስራ አፈጻጸም መለኪያዎች አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ ሂሳብ ዓመቱን በጥሩ ውጤት ማጠናቀቅ ችሏል።
በ2024/25 የሂሳብ ዓመት የባንካችን ጠቅላላ ገቢ በ77 በመቶ እድገት በማሳየት ብር 64 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን በዓመቱ ያልተጣራ ትርፍ ከግብር በፊት ብር 22 ቢሊዮን በላይ ለማትረፍ ችሏል።
በተጠናቀቀዉ የሂሳብ ዓመት የባንኩ ተቀማጭ ሂሳብ ብር 332 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት (IFB) ድርሻ ብር 37.3 ቢሊዮን ወይም 11.24 በመቶ ይይዛል።
በተያያዘም ባንካችን እ.ኤ.አ በ2024/25 የሂሳብ ዓመት ከ2 ቢልዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማሰባሰብ የቻለ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንፃር ሲታይ የ25 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
አዋሽ ባንክ በሂሳብ ዓመቱ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች በድምሩ ከ219 ቢሊዮን ብር በላይ ብድሮችን የሰጠ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ20 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
ባንኩ በሂሳብ ዓመቱ ካቀረበው የብድር መጠን ውስጥ ከብር 16.6 ቢሊዮን በላይ የተሰጠው በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለታቀፉ ከ14 ሺህ በላይ ደንበኞች ሲሆን፤ በተመሳሳይም መካከለኛ እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በእጅጉ የሚጠቅም የተለያዩ አገልግሎቶችን በማቅረብ እየሰራ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር መስመር (MESMER) በተሰኘ ፕሮግራም ወደ 12 ሺህ ለሚጠጉ ማይክሮ፣ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ባንኩ ከብር 1.3 ቢልዮን በላይ ፋይናንስ አድርጓል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሁሉን አካታች እና ተደራሽ በሆነዉ አዋሽ ለሁሉ በተሰኘው የዲጂታል የብድር አገልግሎት አማካኝነት ከ301 ሺህ በላይ ለሆኑ ደንበኞች ያለ ምንም ማስያዣ ከ493 ሚሊዮን ብር በላይ በሂሳብ ዓመቱ የዲጅታል ብድር ተሰጥቷል።
በሂሳብ አመቱ በዲጂታል የተከናወነው የገንዘብ ዝውውር መጠን አንድ ትሪሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ ይህም በሂሳብ ዓመቱ በባንኩ ከተከናወኑ የገንዘብ ዝውውሮች ከ76 በመቶ በላይ ድርሻ ነበረው።
አዋሽ ባንክ በየዓመቱ የተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ችግሮች ሲከሰቱ ቀድሞ በመድረስ ህዝባዊ ወገንተኝነቱን ያስመሰከረ ሲሆን፣ በሂሳብ ዓመቱ በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ለተጋለጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች፤ ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለአካባቢ ጥበቃ እንዲሁም ለተለያዩ የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በአጠቃላይ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለኅብረተሰቡ ያለዉን ወገንተኝነት አስመስክሯል።
ባንኩ በሂሳብ አመቱ የባንኩ ጠቅላላ ካፒታል አምና ከነበረበት የ10 ቢሊዮን ወይም የ37 በመቶ እድገት በማስመዝገብ በጁን 30፣2025 ከብር 37 ቢሊዮን በላይ ደርሷል።
አዋሽ ባንክ በሂሳብ ዓመት 2024/25 ለተለያዩ የግብር ዓይነቶች በአጠቃላይ ከብር 10.8 ቢሊዮን በላይ በመክፈል ለሃገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል።
አዋሽ ባንክ!

Mar 09, 2026 - EXCHANGE Rate
CurrencyCash and Remittances through AgentsTransaction
BuyingSellingBuyingSelling
USD USD153.2439156.3088153.0141156.0744
GBP GBP207.4951211.6450207.4951211.6450
EUR EUR181.4794185.1090181.4794185.1090
JPY JPY1.01121.03141.01631.0366
SAR SAR43.084043.945743.587744.4595
AED AED44.022344.902744.539545.4303
CAD CAD111.3935113.6214112.6983114.9523
CHF CHF195.6127199.5250197.8906201.8484
NOK NOK14.737615.032413.697013.9709
DKK DKK23.213723.678023.485123.9548
SEK SEK17.027717.368317.226817.5713