አዋሽ ባንክ እና የጤና ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የሥራ ውል ስምምነት ተፈራረሙ

የኢፌዲሪ የጤና ሚኒስቴር እና አዋሽ ባንክ የዲጂታል ጤና ክፍያን በአዋሽ ባንክ የዲጂታል ባንክ አማራጮች ለማስጀመር የሚያስችል የሥራ ውል ስምምነት በዛሬው እለት በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ተፈራርመዋል፡፡
የፊርማ ሥነ-ስርዓቱ በጤና ሚኒሴቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰሀረላ አብዱላሂ እና በአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ፀሐይ ሽፈራዉ መካከል ተካሂዷል፡፡
በስምምነቱም የጤና ነክ ክፍያዎች ባንኩ ያሉትን ዘመኑን የዋጁ የዲጂታል አማራጮችን በማቅረብ በጤና ተቋማት ማለትም በሆስፒታሎች እና በጤና ጣቢያዎች ላይ የሚደረጉ ክፍያዎችን በማዘመን ቀላል እና ለሁሉም ምቹ በሆኑ የዲጂታል አማራጮች ክፍያዎችን እንዲከፍሉ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ ሚኒስትር ዴኤታዋ ክብርት ወ/ሮ ሰሀረላ አብዱላሂ በንግግራቸው እንደገለጹት የጤና ዘርፍን ለማሻሻልና አገልግሎቶችን ዲጂታል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው አንጋፋው አዋሽ ባንክ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት በእጅጉ እንዲስፋፋና እንዲጎለብት እየተጫወተ ያለዉን ሚና እጅግ አበረታች እና ዕዉቅና የሚሰጠዉ መሆኑን ተናገረዋል፡፡
የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራዉ በበሉላቸው ጤና ሚኒስቴር ይህን አብሮ የመስራት እድል ስለሰጣቸው ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይም ባንኩ ከበርካታ ተቋማት ጋር በተለያዩ ዘርፎች ላይ ምቹ እና ቀልጣፋ አገልግሎቶችን መስጠት የሚያስችሉ የዲጂታል አገልግሎት አማራጮችን በማቅረብ ላይ ይገኛል ብለዋል።
አዋሽ ባንክ!

Mar 12, 2026 - EXCHANGE Rate
CurrencyCash and Remittances through AgentsTransaction
BuyingSellingBuyingSelling