በግል ባንክ ኢንዱስትሪ ፈር ቀዳጅ በመሆን በአምስት ቅርንጫፎች ስራ የጀመረው አዋሽባንክ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት ዛሬ ታህሳስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ጃርሶ ወረዳ ኤጀርሰ ጎሮ ከተማ1000ኛ ቅርንጫፉን የባንካችን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሃይ ሽፈራውን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት አካላት እና እንግዶችበተገኙበት በይፋ አስመርቋል።አዋሽ ባንክ በመላ አገሪቱ ቅርንጫፎቹን በማስፋፋት ህብረተሰቡ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎቶችንበአቅራቢያው እንዲያገኝ በማስቻል በአሁን ወቅት የደንበኞቹን ብዛት ከ16.3 ሚሊዮን በላይ አድርሷል፡፡ በተጨማሪም ለአገሪቱ የኢኮኖሚዕድገት እና ለሕብረተሰቡ የኑሮ መሻሻል የበኩሉን አስተዋጽኦ በማበርከት በፋይናንስ ኢንዱስትሪው የበኩሉን አስተዋፅኦ በመወጣት ላይእንደሚገኝ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሃይ ሽፈራው በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ገልፀዋል፡፡ ባንኩ ከመ ደኛው የባንክ አገልግሎት ሰጪ ቅርንጫፎች በተጨማሪ ደንበኞችን ማዕከልባደረጉ ከወለደ ነጻ የባንክ አገልግሎትና በዲጂታል ቅርንጫፎች (e-Branch) በመታገዝ ዘመኑን የዋጁ ቀልጣፋ አገልግሎቶችን እየሰጠይገኛል። አዋሽ ባንክ የጃርሶ ቅርንጫፍን ከመክፈት በተጨማሪ የአካባቢውን ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለሀገር ብዙ ውለታ የዋሉ የሀገር ባለውለታዎች ላፈራው ለጃርሶ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ግምታቸው በብር አንድሚሊዮን ሶስት መቶ ሺህ ዋጋ የሚያወጡ ብዛታቸው 25 የሆኑ ኮምፒዩተሮችን አበርክቷል። ከዚህም በተጨማሪ የኤጀርሳ ጎሮ ከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ አናየአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርግ የከርሰ ምድር የውሃ ቁፋሮ ፕሮጀክት ለማከናወን ባንኩ በጀት የመደበ ሲሆን የፕሮጀክቱማስጀመሪያ የመሰረተ ድንጋይም በዛሬው እለት ተቀምጧል።



















