የ7ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና እና ሽልማት ሥነ-ሥርዓት በትናንትናው እለት በአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማእከል በተካሄደበት ወቅት ባንካችን ከፍተኛ ግብር በታማኝነት በመክፈሉ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእዉቅና ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡ አዋሽ ባንክ ከጊዜ ወደ ጊዜ የአገልግሎት አድማሱን እያሰፋ ዘመኑን የዋጀ ሁሉን አካታች የሆነ አስተማማኝ የባንክ አገልግሎቶችን በሰፊዉ ለደንበኞቹ በማቅረብ ላይ ይገኛል:: ባንካችን በሚሰጠው አገልግሎቶች ከሚሰበስበው ታክስና ግብር በዚህ ዓመት ብቻ ከ10 ቢሊየን ብር በላይ ግብር ለመንግስት ገቢ በማድረግ፣ ለሀገራችን የኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል። እያበረከተም ይገኛል።
አዋሽ ባንክ የአገልግሎት አድማሱን ከማስፋቱም ባሻገር የወገኖቻችንን ህይወት ለማሻሻል የሚረዱ ተግባራትን በሃላፊነት መንፈስ በመወጣት ላይ ይገኛል። ለአብነት ያህል በ2017 ዓ.ም የማህበራዊ ሃላፊነቱን በመወጣት ረገድ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የበኩሉን አስተዋፅኦ የተወጣ ሲሆን ወደፊትም አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
አዋሽ ባንክ ይህን ተቋማዊ ግዴታውን የመወጣት ተግባር ወደፊትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማረጋገጥ ይወዳል፡፡
አዋሽ ባንክ!


















