የማህበራዊ ሃላፊነቱን በመወጣት የሚታወቀው አዋሽ ባንክ፣ የረመዷን ወር ፆምን ምክንያት በማድረግ በሸራተን ሆቴል ባዘጋጀው የኢፍጣር መርሀ-ግብር ላይ ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችእና ተቋማት የ 23.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።
በዚህም መሰረት፡
- ለኢትዮ ጠቢብ ጠቅላላ ሆስፒታል ለ24 የኩሌሊት ታካሚዎች ለአንድ አመት የኩላሊት እጥበት የሚውል 6.9 ሚሊዮን ብር
- ለአሚን ጠቅላላ ሆስፒታል ለ12 የኩሌሊት ታካሚዎች ለአንድ አመት የኩላሊት እጥበት የሚውል 4.6 ሚሊዮን ብር
- ለአወሊያ እርዳታ እና ልማት ድርጅት ማጠናከሪያ የሚውል 5 ሚሊዮን ብር እና
- ለታላቁ አንዋር መስጂድ የከርሰ ምድር ውሃ ቁፋሮ የሚውል 7 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።
ይህም ድጋፍ በተቋማቱ አማካኝነት ለሚረዱ እና ድጋፍ ለሚሹ ማህበረሰብ ክፍል እንዲደርስ ታሳቢ የተደረገ ነው።



















