ባንካችን በዛሬው እለት በዋና መ/ቤት ባካሄደው የሽልማት አሰጣጥ መርሐግብር ላይ በንግድ ስራ የተሰማሩ የመርቻንት ካሸሮች የአዋሽ ባንክ ፖስ ማሽንን በስፋት ደንበኞች እንዲጠቀሙ በማድረግ የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገባቸው ከብር 5,000 እስከ 20,000 የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት አበርክቶላቸዋል፡፡
አዋሽ ባንክ ላለፉት 30 ዓመታት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፉ እና ዘመኑን የዋጁ የባንክ አገልግሎቶችን ተደራሽ አድርጓል። በዚሁም ደንበኞች ግብይቶቻቸውን ያለምንም ውጣ ውረድ ለመፈፀም እንዲችሉ የአዋሽ ባንክ POS ማሽኖችን በመጠቀም ያለ ጥሬ ገንዘብ በካርዳቸው ብቻ እንዲገበያዩ አስችሏል። አገልግሎቱም በተለያዩ የገበያ ማዕከላት፣ በካፍቴሪያ፣ በሱፐርማርኬት፣ በፋርማሲ እና በሌሎች የንግድ ተቋማት ማግኘት እንዲችሉ ተደራሽነቱን በማስፋት ላይ ይገኛል፡፡



















