ከምስረታው ጀምሮ የማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አንፃር ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ የሚገኛው አዋሽ ባንክ በሠራተኛና ክህሎት ሚኒስቴር ሥር ከሚገኘው የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት (EDI) ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ከሚገኙና ከተለያዩ ማዕከላት ለተውጣጡ ከ100 በላይ ለሚሆኑ ለጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የአቅም ግንባታ የቢዝነስ ክህሎት ስልጠና በግዮን ሆቴል በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህ ፕሮገራም በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚተገበር ይሆናል፡፡ ባንኩ በቀጣይም ዘርፉን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
አዋሽ ባንክ!



















