አዋሽ ባንክ ከማስተር ካርድ ፋዉንዴሽን እና ፈርስት ኮንሰልት ጋር በመተባበር MESMER በተሰኘው የብድር ፕሮግራም ላለፉት ሶስት ዓመታት በብዙ ሺህ ለሚቆጠሩ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በፋይናንስ አቅርቦት፣ እንዲሁም የፋይናንስ እውቀታቸዉን ከፍ ለማድረግ በቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ላይ ስልጠናዎችን ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣ የብድር ዕድሎችንም አመቻችቷል፡፡
መስመር ዲጂታል የብድር አገልግሎት (Digital Loan) የመካከለኛ እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞቹን የብድር አገልግሎት በማዘመን በአዋሽ ብር ፕሮ በኩል ወይም ወደ *901# ላይ በመደወል አገልግሎቱን ማግኘት የሚያስችል አሰራር ነው።
የመስመር ፕሮግራም ከተጀመረበት እስካሁን ድረስ ከ66,000 በላይ መካከለኛ እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አገልግሎቱን ለማግኘት በባንኩ በኩል ያመለከቱ ሲሆን፣ ከነዚህም ውስጥ ከ13,000 በላይ የሚሆኑ ኢንተርፕራይዞች በድምሩ ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ በአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሲሆኑ ከእነዚህም ዉስጥ 32 በመቶው ሴት ኢንተርፕሬነሮች ናቸዉ።
በተጨማሪም የአመልካቾችን የብድር ጥያቄዎች ለማቀላጠፍ ይረዳ ዘንድ 1,276 የብድር ኦፊሰሮችን በመመደብ ለMESMER ፕሮግራም ስኬት ከፍተኛ ድጋፍ ተደርጓል። በዚህ አፈጻጸሙ ባንኩ በተጠቃሚዎቹ ዘንድ በመድረስና በማገልገል ጉልህ ሚና ተጫዉቷል፡፡
አዋሽ ባንክ!



















