አዋሽባንክ የደንበኞች ሳምንትን በማክበር ላይ ይገኛል

አዋሽ ባንክ ‘’ለላቀ የደንበኞች እርካታ እንተጋለን’’ በሚል መሪ ቃል ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የደንበኞች ሳምንት ከዛሬ የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች በደማቅ ሁኔታ ማክበር ጀምሯል፡፡
በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በታደሙበት የደንበኞች ሳምንት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ- ስርዓት ላይ በመገኘት ለደንበኞች መግለጫ የሰጡት የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፀሀይ ሽፈራው እንደገለፁት በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የአዋሽ ባንክ ደንበኞች ለባንኩ እድገት እና ዘላቂነት ላበረከቱት አስተዋፅኦ ያላቸውን ታላቅ አክብሮት በመግለፅ በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከደንበኞች የሚነሱ ማንኛውም አይነት ሀሳብ እና አስተያየት በመቀበል ለተግባራዊነቱም አበክረው እየሰሩ እንደሚገኙ አመላክተዋል፡፡

Mar 12, 2026 - EXCHANGE Rate
CurrencyCash and Remittances through AgentsTransaction
BuyingSellingBuyingSelling