ሐምሌ 25፣2017 ዓ.ም
አዋሽ ባንክ የደንበኞቹን ፍላጎት ከሟሟላት ጎን ለጎን በሃገራችን ኢኮኖሚ እድገት ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ቀጥሏል። በዚህም መሰረት በሃገራችን ውስጥ የሚታየውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍና በውጭ ምንዛሬ አደላደል ዙሪያ ግልጽነት እንዲፈጠር የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በመወጣት ላይ ይገኛል። ከዚሁም ጋር ተያይዞ እ.ኤ.አ ከሐምሌ 1፣2025 እስከ ሐምሌ 31፣2025 ድረስ ባንኩ ከደንበኞቹ ከቀረቡ ጥያቄዎች ውስጥ አብዛኛውን ጥያቄዎች ያስተናገደ ሲሆን በዚህም በሐምሌ ወር ብቻ በድምሩ ከ125 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ለደንበኞች እንደ ጥያቄያቸው አቅርቧል።
በዚሁ ወር ባንኩ ለደንበኞች ካቀረበው የውጭ ምንዛሪ ውስጥ ከ70 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ለነዳጅ እና ቀሪውን ከ55 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ወደ ሃገራችን የሚገቡ ስልታዊ ሸቀጦች (Strategic Commodities) የሰጠ ሲሆን ለትምህርት እና ለህክምና የመሳሰሉ ክፍያዎችንም ቅድሚያ በመስጠት የውጭ ምንዛሪ ድልድል ማድረጉን ቀጥሏል።
አዋሽ ባንክ የደንበኞቹን የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት ለማርካት የሚያስችል አቅርቦት ያለው ሲሆን በቀጣይም ባንኩ በእጁ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ በስፋት እያቀረበ የሚቀጥል መሆኑን በአክብሮት ይገልጻል።
አዋሽ ባንክ!
















